GERD Final Legacy Uncategorised አባይን በልጄ፣ የመጪው ትውልድ አሻራ

አባይን በልጄ፣ የመጪው ትውልድ አሻራ

አባይን በልጄ፣ የመጪው ትውልድ አሻራ post thumbnail image

ጤና ይስጥልን

በፓሪስ የኤፌዲሪ ሚሲዮን ከነገ ማክሰኞ ወይም 10th of June 2025 ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉ ቀናት ለአንድ ወር
የሚቆይ አባይን በልጄ፣ የመጪው ትውልድ አሻራ በሚል መሪ ቃል የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጨረሻ የቦንድ
ሸያጭ፣ የስጦታ፣ የልጆች አሻራ የማኖር መርሃ ግብር አዘጋጅቷል። በመሆኑም፣

  • በፓሪስ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አንድ ጉርድ ፎቶ፣ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ
    ወይም ፓስፖርት በመያዝ በኢምባሲያችን በአካል በመገኘት የመጨረሻ አሻራ ማኖር፣
  • ክፓሪስ ውጭ ባሉ ከተሞች እና በስፔን የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የመጨረሻ አሻራ
    ለማኖር ለዚሁ ጉዳይ ለተመደቡ 0633 901713/ 0773 791704 በመደወል በምታገኙት መረጃ መሰረት መሳተፍ፣
  • ያለተጨማሪ የቦንድ ግዥ ቀደም በተገዙ እና የመክፈያ (Matured Date) ግዚያቸው የደረሱ ቦንዶችን ማራዘም፣
  • በወላጆቻቸው ወይም በአሳዳጊዎቻችው በኩል በስማቸው ቦንድ ወይም ስጦታ ለሚበረከትላቸው ልጆች
    በኤምባሲው በማስታወሻነት የሚቀመጥ ልዩ የልጆች አሻራ የማኖር እድል መመቻቸቱን ኢምባሲው እያሳወቀ ።

የኢምባሲው አዳራሸ በተጠቀሱት ቀናት ለዚሁ ጉዳይ ክፍት መደረጉን እያሳወቅን በዚህ ታሪካዊ ምእራፍ ላይ በራሳችሁ
እና በልጆቻችሁ ስም የመጨረሻ አሻራችሁን እንድታኖሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post